Fana: At a Speed of Life!

የሎጂስቲክ ዘርፍ አፈጻጸም መታወቅ ዘርፉን ለማዘመንና ለውጥ ለማምጣት ያስችላል – ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  የሎጂስቲክ ዘርፍ አፈጻጸም መታወቅ ዘርፉን ለማዘመንና እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚያስችል የትራንስፖርት ሚኒስትሯ  ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ።

የመጀመሪያው አገራዊ የሎጂስቲክ አፈጻጸም ሪፖርት ይፋ በተደረገበት መርሐግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ወይዘሮ ዳግማዊት÷ “የሎጂስቲክ ዘርፍ አፈጻጻም ደረጃ የወጪ ንግድ ስርዓቱን ለመገምገም የሚያስችል ነው” ብለዋል።

የዘርፉ አፈጻጸም መታወቅ የአገራትን ሳቢነት የሚያሳይና የኢንቨስትመንት እድልን የሚፈጥር ነው ያሉት ሚኒስትሯ÷ የአለም ባንክ በየአመቱ የሎጂስቲክ አፈጻጸምን በመገምገም የአገራትን ደረጃ እንደሚያስቀምጥ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያም በ10 አመቱ የትራንስፖርት መሪ ዕቅድ ላይ ሎጂስቲክ ዘርፉን ዋና አካል በማድረግ እየሰራች እንደምትገኝም ጠቅሰዋል።

አለምአቀፋዊ መመዘኛዎችን ያካተተ በአገር በቀል ዕውቀት የተዘጋጀ የሎጂስቲክ አፈጻጸም ለዘርፉ ስኬት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው አመልክተዋል።

አፈጻጸምሙ መታወቁ ዘርፉን ለማዘመንና እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት ያስችላልም ብለዋል።

አክለውም የአፈጻጸሙ መታወቅ በሣይንሳዊ መንገድ ለመመራት፣ ወደ ዲጂታል አገልግሎት ለማደግ፣ የመሠረተ ልማት ግንባታን ለማሳለጥና የመረጃ እጥረትን ለመቀነስ እንደሚያስችልም መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.