Fana: At a Speed of Life!

ዳርፉር በግጭት እና ብጥብጥ እየተናጠች ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ ሁለት ዓመቱ ህዝባዊ ተቃውሞ ኦማር አልበሺርን ከስልጣናቸው በማውረድ ቢጠናቀቅም ዳርፉር ግን አሁንም በግጭት እና ብጥብጥ እየተናጠች ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት የምዕራብ ዳርፉሯ ዋና ከተማ ኤል ገኒና ጎዳናዎች ተቃውሞ በሚያሰሙ ሰዎች ተጥለቅልቀዋል፡፡ ከከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የኪሪንዲንግ ካምፕ ውስጥ በተጠለሉ ተፈናቃይ ሰፋሪዎች ላይ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ሁለት ጊዜ በታጣቂዎች ጥቃት እንደተፈፀመ ተመላክቷል፡፡

ጥቃት ፈፃሚዎቹ በርካታ ቤቶችን ሲያቃጥሉ ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ ነዋሪዎችም ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከአካባቢው መሰደዳቸው ነው የተነገረው፡፡ በከተማዋ መንገዶች ላይ የሸክላ ውጤት ቁሶች፣ጥራጥሬ እና የተለያዩ መገልገያዎች ተበታትነው እንደሚታዩ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.