Fana: At a Speed of Life!

የኳታሩ ባላድና ኩባንያ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኳታሩ ወተት እና የወተት ውጤቶች አምራች የሆነው ባላድና ኩባንያ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ::

ኩባንያው በእንስሳት እርባታ፣ በወተትና የወተት ውጤቶች አመራረት፣ የምርት አስተሻሸግ ሂደትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ተመልክተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገራት በዚሁ ዘርፍ በኢንቨስትመንት ለመሠማራት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

በጉብኝቱ ወቅት በኢትዮጵያ ወተት እና የወተት ውጤቶችን ለማምረት አመቺ የኢንቨስትመንት ሁኔታ እንዳለ ዲፕሎማቶቹ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ባላድና ኩባንያ በኳታር በ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ካሬ ሜትር መሬት ላይ በእንስሳት እርባታ እና በወተት ውጤቶች ማምረት የተሰማራ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.