Fana: At a Speed of Life!

በአውስትራሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በበይነ መረብ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በበይነ መረብ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ከድር በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አምባሳደሩ በተለይም በትግራይ ክልል መንግስት ስለወሰደው ሰብዓዊ የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታና ከታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ጋር ባለው ድርድር የኢትዮጵያን አቋም እንዲሁም ኢትዮጵያ በቅርቡ ያካሄደችውን 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ አብራርተዋል፡፡
አምባሳደሩ በዓመቱ የዳያስፖራ አባላቱ ላደረጉት የነቃ ተሳትፎና ለተገኙ ውጤቶች ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የልጆቿን ድጋፍ ይበልጥ የምትፈልግበት ወቅት በመሆኑ ርብርቡ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በውይይቱ ከተሳታፊዎች የተሰጡ ግብዓቶችን በመውሰድ በቀጣይ የበለጠ ውጤት ለማምጣት መስራት እንደሚገባ ከመግባባት ላይ ተደርሷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.