Fana: At a Speed of Life!

የናይል ተፋሰስ ሀገራት የሚሳተፉበት የሴካፋ ውድድሩ ለህዳሴው ግድብ ገጽታ ግንባታ መጠቀም ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው የናይል ተፋሰስ ሀገራት የሚሳተፉበት የሴካፋ ውድድሩ ለህዳሴው ግድብ ገጽታ ግንባታ መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ።
የምስራቅና የመካከለኛው አፍሪካ ሀገራት (ሴካፋ) ውድድር ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተገምግሟል።
የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹ የፌዴራል የስፖርት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የ6 ንዑሳን ኮሚቴዎች የስራ ዝርዝር ቀርቦ በባህር ዳር ከተማ ነው የተገመገመው።
በግምገማው አስተናጋጁ የአማራ ክልል ተወዳዳሪ ሀገራትን ተቀብሎ ለማስተናገድ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
በግምገማው ላይ የተገኙት የስፖርት ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እየተሰራ ያለው የቅድመ ዝግጅት ስራ በከፍተኛ ትኩረት ተይዞ እየተሰራ በመሆኑ ደስታቸውን ገልጸዋል።
ኃላፊዎች አያይዘውም በዚህ የሴካፋ ውድድር ላይ የናይል ተፋሰስ ሀገራት የሚሳተፉበት ትልቅ ትርጉም ያለው ውድድር በመሆኑ ከህዳሴው ግድባችን ስኬት ጋር በማያያዝ አጋጣሚውን ልንጠቅምበት እንደሚገባና በዚህም ቅኝት ውስጥ ሆነን ሁሉን አቀፍ የተቀናጀና ትርጉም ያለው ስራ ሊስራ እንድሚገባ በጥብቅ አሳስበዋል።
በተጨማሪም የመወዳደሪያና የመለማመጃ ሜዳዎችን በመመልከት የማስተካከያ ምክረ ሀሳቦችን መስጠታቸውን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
See Translation
16
2 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.