Fana: At a Speed of Life!

በትምህርት ዘርፍ 500 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ መያዙ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ዘርፉ የሰኔ 30 የአረንጓዴ የአሻራ ቀን ችግኝ ተከላ መርሀ ግብርን እያከናወነ ነው።
በዛሬው ዕለት የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮቾ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ቱሉ ኮርማ የእጽዋት ማዕከል የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።
ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የተተከሉት ችግኞች ሀገር በቀል እጽዋት ዝርያዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በአረንጓዴ አሻራ የሚተከሉ ችግኞችን ከመትከል ባሻገር እንዲጸድቁ ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
ዛሬ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በተጨማሪ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ተማሪዎችና መምህራን እንደሚሳተፉም ነው የተነገረው።
በፈተና ላይ የሚገኙ ተማሪዎችም ፈተና እንደጨረሱ ከመምህራኖቻቸው ጋር በመሆን በቀጣዮቹ ቀናት ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን እንደሚያኖሩም ተገልጿል።
”ኢትዮጵያን እናልብስ ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራን የማኖር ስነ ስርዓት ባጠቃላይ ከ500 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል እቅድ መያዙን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.