Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ – ሩሲያ 11ኛው ወታደራዊ የቴክኒክ ትብብር የጋራ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ – ሩሲያ 11ኛው ወታደራዊ የቴክኒክ ትብብር የጋራ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው የምክክር መድረኩ÷ የኢትዮጵያን እና ሩሲያን ወታደራዊ ቴክኖሎጂ፣ ክህሎት እና እውቀት ማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ ÷ ሁለቱ ሀገራት ከ1898 ጀምሮ በዲፕሎማሲ ፣ በወታደራዊ ፣ በኢኮኖሚ ፣ በፖለቲካ እና በማህበራዊ መስክ ታሪካዊና ጠንካራ ግንኙነት ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ እና ም/ጠ/ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተው ከመከሩ ወዲህ የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ጥብቅ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል ፡፡
በህግ ማስከበር ዘመቻው ሩሲያ የውስጥ ጉዳያችን እንደሆነ አቋም መያዟ እንዲሁም በ6ኛው ምርጫ ፣ በታላቁ ህዳሴ ግድብና በሌሎችም ሀገራዊ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ጎን ቆማ ወዳጅነቷን በማሳየቷ ሚኒስትር ደኤታዋ ምስጋና አቅርበዋል ፡፡
የዚህን ስብሰባ ውጤትንም የሁለቱን ሀገሮች የጋራ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ተግባራዊ እንደሚደረግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
በሩሲያ ፌዴሬሽን የወታደራዊ የቴክኒክ ትብብር ምክትል ዳይሬክተር ፑንቹክ አናቶሊ በበኩላቸው ÷ ሀገራቱ የቆየ ወዳጅነት እንዳላቸው በመግለጽ በወታደራዊ መስክ ብዙ የኢትዮጵያ መከላከያ አባላት በሩሲያ ስልጠና መውሰዳቸውን አንስተዋል፡፡
የመከላከያ ኢንዱስትሪ እና ደጀን አቭዬሽንን የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ እየተደረገ ያለውን ስራ በጋራ እንደሚያጎለብቱም መናከራቸውንም ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.