Fana: At a Speed of Life!

ከምርጫው በፊት ሳጥን የከፈቱ 6 የምርጫ አስፈፃሚወች በ7 ወር ቀላል እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከምርጫው በፊት ሳጥን የከፈቱ 6 የምርጫ አስፈፃሚዎች በ7 ወር ቀላል እስራት መቀጣታቸውን በደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ገለጸ።
ፍድር ቤቱ ሰኔ 29ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው ከምርጫ ቀን በፊት ታዛቢዎች በሌሉበት መከፈት የማይገባውን የምርጫ የድምፅ መስጫ ወረቀት የያዘውን ሰማያዊ የፕላስቲክ ሳጥን ቁልፍ የከፈቱ 6 የምርጫ አስፈፃሚዎች በ7 ወር ቀላል እስራት እንዲቀጡ የወሰነው፡፡
ተከሳሾች ድርጊቱን መፈፀማቸውን በሰጡት የእምነት ቃል ለወረዳው ፍርድ ቤት አምነዋል፡፡
ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ምስክር ማሰማት ሳይጠበቅበት የወንጀሉን አፈፃፀም ሁኔታና የደረሰውን ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ተከሳሾችን ከጥፋት ያስተምራል ለሌሎችም ያስተምራል ያለውን እያንዳንዳቸው በ7 ወር ቀላል እስራት እንድቀጡ ወስኗል፡፡
በይከበር አለሙ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.