Fana: At a Speed of Life!

ፓስፖርት ለመውሰድና ለማደስ ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ መጓተት ለአላስፈላጊ እንግልት እንደዳረጋቸው ተገልጋዮች ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ፓስፖርት ለመውሰድና ለማደስ የሚሰጠው የአገልግሎት መጓተት ለአላስፈላጊ ወጭና ለእንግልት እንደዳረጋቸው ተገልጋዮች ተናግረዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በኤጀንሲው የፓስፖርት ስርጭት በሚደረግበት ስፍራ ባደረገው ቅኝት ረጃጅም ሰልፎችን ተመልክቷል፡፡
ህገ ወጥ ደላሎች በተቋሙ አሰራሩ ውስጥ ጣልቃ በመግባት በ25 ሺ ብር ክፍያ በአጭር ቀን ፓስፖርት በእጅ እንዲገባ እናደርጋለን በሚል በኤጀንሲው በር ላይ ተገልጋዮችን ሲያዋክቡም ለመታዘብ ተችሏል።
በኤጀንሲው አካባቢ ባሉ ንግድ ቤቶችም ለህገወጥ ስራ የሚያግባቡ ከሰራተኞች ጋር ግንኙነት አለን የሚሉ ግለሰቦች መኖራቸውንም ታዝበናል።
የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል÷ የፓስፖርት ስርጭት በፖስታ አገልግሎት አንድ ማዕከል ብቻ መሰጠቱ በተገልጋዮች ዘንድ መጉላላቱን መፍጠሩን ተናግረዋል።
አገልግሎቱን እናሳልጣለን በሚል የሚሰሩ ህገ ወጥ ደላሎችን ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ÷ ለዚህም አገልግሎቱን ወደ ዲጂታል ለመቀየር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በህገ ወጥ ደላሎች የሚያጭበረበሩ ተገልጋዮች መኖራቸውን በመጥቀስም በድርጊቱ የሚሳተፉት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ከንግድ ቢሮ በቅንጅት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.