የሀገር ውስጥ ዜና

በሀገር ውስጥና በውጭ ያለን ኢትዮጵያውያን አንድና ብዙ ሆነን በብዙ መስኮች ለማሳካት እንነሣ – ጠ/ሚ ዐቢይ

By Meseret Awoke

July 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሀገር ውስጥና በውጭ ያለን ኢትዮጵያውያን አንድና ብዙ ሆነን በብዙ መስኮች ለማሳካት እንነሣ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ‘‘ብዙ ሆነን፣ ብዙ ነገሮችን በብዙ መስኮች ለማሳካት እንነሣ’’ ብለዋል ።

‘‘በሀገር ውስጥና በውጭ ያለን ኢትዮጵያውያን፣ ሁላችንም ለኢትዮጵያ ከልብ ተነሥተን፣ የክረምቱን ግብርናና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ አረንጓዴ ዐሻራን፣ 2ኛው ዙር የሕዳሴ ግድብን ሙሌት፣ ሉዓላዊነታችንን ማስጠበቅን፣ ዲፕሎማሲያችንን፣ በአንድ ጊዜ፣ አንድና ብዙ ሆነን፣ በብዙ መስኮች ለማሳካት እንነሣ’’ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!