Fana: At a Speed of Life!

በግብፁ ፕሬዚዳንት ላይ ተቃውሞ እንዲነሳ ሲቀሰቅስ የነበረው መሀመድ አሊ ራሱን ከፓለቲካ አገለለ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በመልቀቅ በግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ላይ የተወሰነ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ ምክንያት የነበረው የቀድሞው የመከላከያ ኮንትራክተር መሀመድ አሊ ራሱን ከፓለቲካ አገለለ።

የንግድ ሰው መሀመድ አሊ ራሱን ከፓለቲካ ማግለሉን ያስታወቀው በፈረንጆቹ የ2011 በግብፅ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ዘጠነኛ ዓመት ለማሰብ የጠራው መንግስታዊ ተቃውሞ ስኬታማ ሳይሆን መቅረቱን ተከትሎ ነው።

ፕሬዚዳንት አል ሲሲን እና መከላከያውን በሙሰኝነት የሚከሰው ግለሰቡ በተንቃሳቃሽ ምስል ባስተላለፈው መልዕክት ከአሁን በኋላ የፌስቡክ ገፁን እንደማይጠቀም ገልጿል።

አሁን ላይ ወሳኝ ጊዜ ላይ እገኛለሁ ያለው በስፔን ስድት ላይ የሚገኘው የንግድ ሰው ለግብጻዊያን  እየተፈፀመ ያለውን የሙስና አይነት እና የእስር ዘመቻ አሳይቻለሁ ብሏል፡፡

በዚህ ጉዳይ ከአሁን በኋላ ማውራት አስፈላጊም አይደለም ሲል ተናግሯል፡፡

በቅርቡ ላቀረበው ጥሪ ከግብፃዊያን የተሰጠው ምላሽ  ዜጎች ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ተመችቷቸዋል አልያም እርምጃ ይወሰድብናል የሚል ከፍተኛ ስጋት  ተፈጥሮባቸዋል ሲል ነው የተናገረው፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.