Fana: At a Speed of Life!

በሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ።
ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው በሐምሌ ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ ምርት ውጭ ያሉ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን ጠቁሟል።
የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን በሚመለከት የዓለም ነዳጅ ዋጋ መሰረት በማድረግ እንዲሰላ መደረጉን አመልክቷል።
በዚህ መሰረት በሐምሌ ወር የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ አዲስ አበባ ላይ በሊትር ሲሸጥበት ከነበረው 48 ብር 22 ሳንቲም ወደ 51 ብር ከ76 ሳንቲም ከፍ እንዲል ተደርጓል።
በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ እንደሚችልም መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.