Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት በጉለሌ እጽዋት ማዕከል የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

“ኑ አዲስ አበባን እናልብስ” በሚል መሪ ቃል በከተማዋ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴን ጨምሮ የምክር ቤቱ አባላት በጉለሌ እጽዋት ማዕከል በመገኘት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተክለዋል፡፡

በተመሳሳይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ከከተማዋ ከ11 ክፍለ ከተሞች በተውጣጡ የብሎክ አደረጃጀት አመራሮች እና ነዋሪዎች ጋር በመሆን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ችግኝ ተክለዋል፡፡

በተጨማሪም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በየካ ሚሊኒየም ፓርክ ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማም በመገኘት ከክፍለ ከተማው አመራሮች እና ነዋሪዎች ጋር የአረንጓዴ አሻራ አሳርፈዋል፡፡

በዘንድሮ የክረምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ 7ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡

በመርሃ ግብሩ የተለያዩ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መስሪያቤት እና የክፍለ ከተሞች አመራሮች፣ ሰራተኞች የሃይማኖት አባቶች፣ ተማሪዎች፣ የጸጥታ አካላት እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ከአዲስ አበባ ፕረስ ሴክሬታርያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.