Fana: At a Speed of Life!

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች አቀባበል አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለ4 ሺህ 103 ተማሪዎች አቀባበል አደርጓል፡፡
በዩኒቨርስቲው አስተባባሪነት የአካባቢው ማህበረሰብ፣ከተማ አስተዳደሩ፣አባገዳዎች እና የሐይማኖት አባቶች በጋራ ለተማሪዎች አቀባበል አድርገዋል፡፡
ከሰኔ 28 እሰከ ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም የተደረገው አቀባበል በመልካም ሁኔታ መጠናቀቁን የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳን ዶክተር ሀሰን ዩሱፍ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ ተማሪዎች በመቻቻል እና የአብሮነት ባህል ማጠናከር አለባቸው ያሉት ዶክተር ሀሰን ተመሳሳይ አቀባበል በጊምቢ እና ሻምቡ ካምፓሶች እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በኤፍሬም መልካሙ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.