የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ክልል በበጀት አመቱ  64 ሺህ ሜትሪክ ቶን ቡና ለአለም ገበያ መቅረቡን ተገለጸ

By Meseret Demissu

July 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በበጀት አመቱ  64 ሺህ ሜትሪክ ቶን ቡና ለአለም ገበያ መቅረቡን

ተገልጿል።

የ2013 ዓ.ም የመኸር የቡና ችግኝ  ተከላ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀግብር በጌድኦ ዞን ተጀምራል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ንቅናቄዉን ባስጀመሩበት ወቅት ÷አርሶ አደሮቻችን የኢትዮጵያ ተስፋዎች ናቸው ብለዋል።

በበጀት አመቱ  64 ሺህ ሜትሪክ ቶን ቡና ለዉጪ ገበያ ያቀረበው ክልሉ በቀጣይ 100 ሺህ ሜትሪክ ቶን የመላክ ዕቅድ እንዳለው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ  ጨምረው ገልፀዋል።

ሀገሪቱ የጀመረችው  የብልፅግና ጉዞ የሚረጋገጠው በአርሶ አደሮች ትልቅ አቅም መሆኑን የገለፁት አቶ ርስቱ÷ ሀገር በቀል ዕዉቀቶችን ከአርሶ አደሮቻችን በመውሰድ ከግብርናዉ ሳይንስ ጋር ማቀናጀት ዉጤት  ያመጣል ብለዋል።

በመቅደስ  አስፋው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!