Fana: At a Speed of Life!

በጀርመን የዴልታ ኮሮና ቫይረስ ዝርያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከሰተ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በጀርመን በመተላለፍ ባህሪው አደገኛ የሆነ የዴልታ ኮሮና ቫይረስ ዝርያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከስቷል፡፡

የጀርመን የጤና ባለሙያዎች እንዳስታወቁት፥ የዴልታ ኮሮና ቫይረስ ቀደም ብሎ ከታወቀው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ የመተላለፍ አቅሙ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነና 59 በመቶ የሚሆኑት አዳዲስ ተጠቂዎችም በዚሁ ቫይረስ የተያዙ እንደሆነ ነው፡፡

የጀርመን ጤና ሚኒስትር ጂን እስፓን እንደገለፁት፥ ቀጣዩ ጊዜ የበዓል ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የዴልታ ዝርያ ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከ 70 እስከ 80 በመቶ ሊደርስ እንደሚችል ነው፡፡

የሮበርት ኮች ኢንስቲቲዩት በቀጣይ በሀገሪቷ የተለያዩ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች የመከሰት እድላቸው ከ90 በመቶ በላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

እንደ ኢንስቲቲዩቱ ቫይረሱን የመከላከል አቅም ለማጎልበት ከዚህ ቀደም የአስትራ ዜኒካ ክትባት የመጀመሪያ ዶዝ የወሰዱ ዜጎች በቀጣይ የፋይዘር/ባዮቴክ ወይም ሞደርና ክትባት ቢወስዱ ጥሩ ውጤት ይኖረዋል ብሏል፡፡

በሃገሪቱ እስከባለፈው ማክሰኞ ድረስ 47ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች የኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያ ዶዝ ክትባት የወሰዱ ሲሆን፥ 40 በመቶዎቹ ደግሞ ክትባቱን ሙሉ በሙሉ ወስደው ጨርሰዋል፡፡
ምንጭ፡- አር ቲ ኒውስ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.