Fana: At a Speed of Life!

የማብሰያ ጊዜን የሚቀንስ ማብሰያ “ስቶቭ” እየተመረተ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የደገፈው ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅት የመብሰያ ጊዜን ከ6 ሰዓት ወደ አንድ ሰዓት የሚያወርድ “ስቶቭ” እያመረተ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ድርጅቱ ከቡና አተላና ገለባ፣ ከጫት ገረባ፣ ሳጋቱራና ከመሳሰሉት የቆሻሻ ውጋጆች ሃይል መስራት የሚያስችል እና ይህንን የሚጠቀም ስቶቭ ነው እያመረተ የሚገኘው።
ማብሰያዎቹ ከአካባቢ ጋር የሚስማሙና ፍጆታን የሚቀንሱ ናቸው የተባለ ሲሆን÷ ድርጅቱ በቀን እስከ 200 የሚደርስ “ቋይቶን” የሚል መጠሪያ የተሰጠውን ስቶቭ የማምረት አቅም ላይ መድረሱ ተነግሯል፡፡
ድርጅቱ የስቶቭን ንድፍ ፣ እቃውን መፈብረክና ለስቶቩ የሚሆን ተቀጣጣይ በአንድ ላይ በማምረት ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት ውስጥ ብቸኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ተቀጣጣዩ ለማብሰያነት ካገለገለ በኋላ ወደ ከሰልነት የሚቀየር ሲሆን ድርጅቱ ይህንን ከሰል ከደንበኛው ድጋሚ በመግዛት ስራ ላይ ያውለዋል ነው የተባለው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ ተቋማቸው ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን የሚያደግፍበት “የጀማሪ ቴክኖሎጂ ድርጅቶች አዋጅ አዘጋጅቶ መፀደቁን እየተጠባበቀ መሆኑንና ይህ አዋጅ እንዲህ ያሉ ችግሮችን እንደሚፈታ መናገራቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.