ዓለምአቀፋዊ ዜና

በአለም በኮቪድ-19 ህይዎታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 4ሚሊየን አለፈ

By Meseret Awoke

July 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 ህይዎታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 4ሚሊየንን አልፏል፡፡

እስካሁን በአለም ከ185 ሚሊየን 974ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥ ከ4ሚሊየን 20ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በበኩላቸው አለም ዓቀፍ የክትባት ዕቅድ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን፥ ዕቅዱን ለማሳካት የሃገራትን ክትባት የማምረት አቅም ለማጎልበት የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዓለም በቫይረሱ አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ፈረንሳይ እና ሩሲያ ቫይረሱ ከጸናባቸው ሃገራት ውስጥ በቅድሚያ ይጠቀሳሉ፡፡

በአንጻሩ ከ170 ሚሊየን 181 ሺህ በላይ ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፡፡

ምንጭ፡-ዎርልድ ኦ ሜትር እና ሲጂቲኤን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!