Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከሜክሲኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ጋር  ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አቶ ደመቀ መኮንን ከሜክሲኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርሴሎ ኢብራርድ ጋር በበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም በአገራቱ መካከል ለረጅም  ዓመታት የዘለቀውን በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ግንኙነትን  አንስተዋል።

በዚህም የትብብር መስኮችን በማስፋት ግንኙነቱን የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግም ተገልጿል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በተደረገ ውይይትም በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት የሚደረገው የሶስትዮሽ  ድርድርን በማስቀጠል በቅን መንፈስ በመደራደር መፍትሄ መስጠት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

አቶ ደመቀ በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ  በተለይም በትግራይ ክልል ተፈፀሙ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን፣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮምሽንና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ተቋም የጋራ ምርመራ እያከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ደመቀ አያይዘውም ይህንን አዎንታዊ ርምጃ ከግምት ያላስገባ ጫና ግን ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ማስረዳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤትያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.