Fana: At a Speed of Life!

ከ250 ዓመታት በፊት የታተመ የመጸሐፍ ቅዱስ ቅጂ ለባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተበረከተ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ250 ዓመታት በፊት የታተመ የመጸሐፍ ቅዱስ ቅጂ ለባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተበርክቷል፡፡
ኪንግ ጀምስ ቅጂ በመባል በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቀው ቀደምት ሙሉ የእንግሊዘኛ የመጸሐፍ ቅዱስ ቅጂ ምንጮች አንዱ የሆነው እ.አ.አ 1769 ላይ የታተመው መጸሐፍ ቅዱስ ከአቶ ሳምሶን መኮንን ጣሰው ቤተሰብ ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ተበርክቷል።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶክተር ሒሩት ካሳው፣ የባሕል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት እና የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ተገኝተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.