Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ሀሰተኛ ብር ሲያትሙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሀሰተኛ ብር ሲያትሙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
በክፍለ ከተማው ሀሰተኛ ብር በማተም በሀገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ ፀጥታና ደህንነት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ቡድኖችና ግለሰቦችን ለአንድ ወር ያህል የመረጃና ክትትል ሥራ ሲሰራ መቆየቱ ተገልጿል፡፡
በዚህም ትናንት ምሽት የሀሰተኛ ብር አታሚዎች ከእነ ሀሰተኛ ብር ኖቶች፣ ማተሚያ ማሽኑ እንዲሁም ከተባባሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል ።
ምክትል ከንቲባዋ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.