በመዲናዋ የሚኖሩ ባለሀብቶች ለመከላከያ ሠራዊትና ለህዳሴ ግድብ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያበረክቱ አስታወቁ
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚኖሩ ባለሀብቶች ለኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትና ለህዳሴ ግድብ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያበረክቱ አስታወቁ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከባለሀብቶች ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በሸራተን አዲስ አየተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተና ጄነራል ባጫ ደበሌ ተገኝተዋል፡፡
በዚህ የውይይት መድረክ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ መከላከያ ሠራዊት ትግራይን ለቆ የወጣው በፖለቲካ ውሳኔ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በትግራይ የተበላሸው መሰረተ ልማት እንዲጠገን ህዝቡም ወደ ልማቱ እንዲመለስ በማሰብ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
ሌተና ጄነራል ባጫ ደበሌ በበኩላቸው÷ ሠራዊቱ ትግራይን ለቆ ሊወጣ የነበረው እነ ስብሀት ነጋ በተያዙበት ወቅት ነበር በኋላ ግን ጊዜያዊ አስተዳደሩን ለማገዝ ይቆይ ተባለ ብለዋል፡፡
ህዝቡ በአራቱም አቅጣጫዎች ከሠራዊቱ ጋር እንዲዋጋ በማድረግ መንግስትን በዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ በማሰብ ወያኔ በቅርቡ ያደረገውን እንቅስቃሴ በጥንቃቄ በመመልከት ህዝቡ ወደ ልቡ እንዲመለስ እድል ለመስጠት በማሰብ ትግራይን ለቀናል ብለዋል ጄነራል መኮንኑ፡፡
ምንም እንኳን ጦሩ ለስትራቴጂ ከትግራይ ቢወጣም በክልሉ ዙሪያ በተጠንቀቅ ነው ያለው ብለዋል ጀነራሉ፡፡
አትጠራጠሩ የመከላከያ ሠራዊት በፈለገው ሰዓት መቀሌ ገብቶ ይወጣል ብለዋል፡፡
ባለሀብቶቹም ለሠራዊቱ እና ለህዳሴ ግድቡ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያበረክቱ አስታውቀዋል፡፡
ለተሰው የሠራዊት አባላት ቤተሰቦችም ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡
ባለሀብቱ የሚያበረክተው ድጋፍ በውይይቱ ማጠቃለያ ይታወቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!