Fana: At a Speed of Life!

የፀጥታው ምክር ቤት የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የልማት እና አፍሪካዊ ጉዳይ መሆኑን ማረጋገጡ ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል ነው-አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የፀጥታው ምክር ቤት የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የልማት እና አፍሪካዊ ጉዳይ መሆኑን ማረጋገጡ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት መሆኑን  ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ  ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች ላይ ጠንካራ ፍተሻና ምርመራ እንደሚደረግም አስታውቋል።

ጉዳዩ ወደ ምክርቤቱ የመለስ እድል እንደሌለው አምባሳደሩ  ገልጸው ÷የግብፅና የሱዳን አማራጭ ልማቱን መደገፍ ብቻ ነውም ብለዋል።

 

የውጭ ገዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መግለጫ እየሰጡ ነው።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመግለጫቸው ለትግራይ ክልል ለሚደረገው የሰብአዊ እርዳታ የአለም አቀፍ ተቋማት የበረራ ፍቃድ ቢሰጥም፤ እያንዳንዱ በረራ ግን መነሻው ከአዲስ አበባ እንደሆነ ገልፀዋል።
በምክርቤቱ ተለዋጭ እና ቋሚ አባል ሀገራት ጋር በተናጠል የተሰራው የማስረዳት ስራ ፍሬ ማፍራቱን አሳይቷል ብለዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኒውዮርክ ያደረጉት ሰልፍ ተፅእኖ መፍጠር የቻለ እና ኢትዮጵያውያኑ ያላቸውን ሀገር ወዳድነት ያሳዩበት ነው ብለዋል።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመግለጫቸው የተጠናጠል ተኩስ አቁሙ ምክንያት አስመልከቶ ለአምባሳደሮችና ለአለምአቀፍ ተቋማት ተወካዮች ማብራሪያ መሰጠቱን ገልጸዋል።
የግብርና ስራውን ህዝቡ በተረጋጋ መንገድ መከወን እንዲችልና ቡድኑ የደህንነት ስጋት አለመሆኑ ዋና ዋና ምክንያቶች መሆናቸውም መገለጹን ተናግረዋል።
ንፁሃንን ሽፋን በማደረግ ቡድኑ ያደረገሰውን ጥቃት አስመልክቶም መገለጹን ተናግረዋል።
ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ፣ የበረራ አገልግሎት መፈቀዱን እና አስፈላጊው ፍተሻ መከናወኑ አስገዳጅ መሆኑም መብራራቱን አንስተዋል።
ቡድኑ ለተኩስ አቁሙ ፈቃደኛ አይደለም ይልቁኑ የማይታሰቡ ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጡ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ብለዋል።
ሌላው በመግለጫው የተነሳው የናይል ተፋሰስ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር የተደረገው ውይይት ነው።
በውይይቱም ግብፅና ሱዳን የግድቡ ጉዳይ ለፀጥታው ምክር ቤት እንዲመራ ማድረጋቸው አግባብ አለመሆኑ ላይ በመግባባት መንፈስ ውይይት ተደርጎበታል ነው ያሉት አምባሳደር ዲና።
ሀገራቱ ለአፍሪካ ህብረት ያላቸውን ንቀት ያሳዩበት መሆኑ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል።
ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አንጻር እስከ ትላንት ድረስ 21 ሺህ 182 ዜጎች በ99 በረራዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል።
ዜጎቹን የመመለሱ ጉዳይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.