Fana: At a Speed of Life!

በስዊድን በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊድን በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡
አደጋው ትናንት ምሽት በመጠኗ ትንሽ በሆነች አውሮፕላን ላይ የደረሰ ሲሆን ዘጠኝ ሰዎችን አሳፍራ እንደነበር ታውቋል፡፡ በአደጋው የዘጠኙም ሰዎች ህይወት ማለፉ እየተነገረ ነው፡፡

አውሮፕላኗ ከእስቶኮልም በስተምዕራብ 160 ኪሎ ሜተር ርቀት ላይ ከሚገኘው የኦሬብሮ አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳች በኋላ ወዲያውኑ እንደተከሰከሰችም ታውቋል፡፡

ምንጭ፡-ሬውተርስ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.