ዓለምአቀፋዊ ዜና

በስዊድን በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ

By Alemayehu Geremew

July 09, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊድን በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ አደጋው ትናንት ምሽት በመጠኗ ትንሽ በሆነች አውሮፕላን ላይ የደረሰ ሲሆን ዘጠኝ ሰዎችን አሳፍራ እንደነበር ታውቋል፡፡ በአደጋው የዘጠኙም ሰዎች ህይወት ማለፉ እየተነገረ ነው፡፡

አውሮፕላኗ ከእስቶኮልም በስተምዕራብ 160 ኪሎ ሜተር ርቀት ላይ ከሚገኘው የኦሬብሮ አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳች በኋላ ወዲያውኑ እንደተከሰከሰችም ታውቋል፡፡

ምንጭ፡-ሬውተርስ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!