Fana: At a Speed of Life!

የጅማ ግብርና ምርምር ማዕከልን 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ችግኝ ተተከለ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል ሰራተኞች የማዕከሉን 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ችግኝ ተከሉ፡፡
የማዕከሉ ሰራተኞች በአረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያን ለማልበስ የታቀደውን እቅድ ለማሳካት በማሰብ 50ኛ ዓመት የምስረታ ምክንያት በማድረግ ችግኝ መትከላቸው ተነግሯል።
በችግኝ ተከላው የተሳተፉ ሠራተኞች ለኢትዮጵያ ልዩ በሆነው በዚህ ቀን እንዲሁም በማዕከሉ 50ኛ አመት መታሠቢያ አሻራቸውን ማሣረፋቸው ትልቅ ደስታ እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።
የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶክተር ግርማ ሀይለ ሚካኤል÷ የጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል ለአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ለጅማ ከተማ 60 ሺህ የቡና ችግኞች ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።
በምርምር ጣቢያው ስር ለሚገኙ አካባቢዎች በአጠቃላይ ከግማሽ ሚሊየን በላይ የቡና ችግኞች ተዘጋጅተዋል ብለዋል።
ከችግኝ ተከላው በኃላ የማዕከሉ ሰራተኞች በጅማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በአቤኔዘር ታየ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.