Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ከ10 ሺህ በላይ ሴቶች ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ህብረ ብሔራዊ እህትማማችነት ለአረንጓዴ አሻራችን”በሚል ከከተማዋ የተውጣጡ ከ1ዐ ሺህ በላይ ሴቶች የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ።
“ኑ ኢትዮጵያን እናልብስ” በሚል የተጀመረው የዘንድሮ የክረምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተካሄደ ነው፡፡
በዚህም የመንግስት ሰራተኞች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ተማሪዎች፣ የጸጥታ አካላት እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አሻራቸውን በማኖር ላይ ይገኛሉ።
በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ከተማ የተውጣጡ ከ10 ሺህ በላይ ሴቶች እና ነዋሪዎች በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ በመገኘት ችግኝ ተክለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈባኤ ወ/ሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ ፣ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበር ወ/ሮ መስከረም አበበ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሀዳስ ኪዱ መሳተፋቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.