Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሚኖሩ ባለሃብቶች ለመከላከያ ሠራዊት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ለማሰባሰብ ቃል ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚኖሩ ባለሀብቶችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ለኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ለማሰባሰብ ቃል ገብተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ከሚኖሩ ባለሀብቶችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በዛሬው ዕለት ውይይት አድርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ባለሀብቶችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችንና ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንዲሉ ኢትዮጵያ ከጀርባዋ የሚያጠቋት እና ለባዕዳን አሳልፈው የሚሰጧት የጥቂት ባንዳዎች እና የእናት ጡት ነካሾች ብቻ ሳትሆን ሚሊየኖች “ከሀገሬ በፊት እኔ ልቅደም” ብለው ከፊት የሚሰለፉላት ልጆች ያላት ሀገር መሆኗንም አውስተዋል፡፡
መድረኩ በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት የታየበት እንደነበር የገለጹት ወይዘሮ አዳነች÷ ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ለማሰባሰብ ስምምነት ላይ መደረሱን አንስተዋል፡፡
ቃል የተገባውን ገንዘብ በአጭር ጊዜ ውስጥ አሰባስቦ ገቢ ለማድረግም ኮሚቴ መዋቀሩ ነው የተገለጸው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.