Fana: At a Speed of Life!

የአየር ንብረት ለውጥ ከየትኛውም አገራት የበለጠ የሚጎዳው ታዳጊ ሀገሮችን ነው-ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል የሚያስፈልገዉን ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
መድረኩ በባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር የተሰበሰበና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል የሚያስፈልገዉን ገንዘብ ለማሰባሰብ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በስብሰባው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአየር ንብረት ለውጥ ከየትኛውም አገራት የበለጠ የሚጎዳው ታዳጊ ሀገሮችን መሆኑን እና የዘመኑ ዋነኛ ችግር ነው ሲሉም አንስተዋል፡፡
ፕሬዝደንቷ ኢትዮጵያ በጣም ተጋላጭ እንደመሆኗ መጠን በተለያዩ የጋራ እና ብሄራዊ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት የህብረተሰቡን የመቋቋም አቅም ለማሻሻል እርምጃ እየወሰደች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ያባባሰ መሆኑን ገልፀው ሁለቱም የተቀናጀ እና ፈጣን የጋራ እርምጃን እንደሚጠይቁ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ያደጉ አገራትም ይህንን ችግር ለመቅረፍ የድርሻቸውን በተቻለ ፍጥነት እንዲወጡ መጠየቃቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.