Fana: At a Speed of Life!

ወደ ትግራይ የሚገቡና ከትግራይ የሚወጡ አውሮፕላኖች አስቀድመው ቦሌ አየር ማረፊያ ማረፍ አለባቸው ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ትግራይ፣ እንዲሁም ከትግራይ ወደ ውጭም ሆነ ወደ አገር ውስጥ አየር ማረፊያዎች የሚደረጉ ሁሉም በረራዎች አስቀድመው ቦሌ አየር ማረፊያ ማረፍይኖርባቸዋል ሲል ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ  ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ ማቆም ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ አካላት ጋር በቅርበት ለመስራት ፍላጎት እንዳለው በድጋሜ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን በሰሜን የአገሪቷ የአየር ክልል በረራ ቢዘጋም የኢትዮጵያ መንግስት ግን ከሰኞ እለት ጀምሮ በትግራይ የሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ ለሚፈልጉ አካላት በሙሉ በረራ ማድረግና እርዳታውን ማድረስ እንደሚችሉ ማስታወቁን መረጃው ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት በረራ እንደከለከለ በማስመሰል  እየወጡ ያሉ አንዳንድ ሪፖርቶች  ግን  ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እያሳሳቱ ይገኛሉ፣ ነገር ግን ሪፖርቶቹ ትክክል አይደሉም  ሲል መረጃ ማጣሪያው ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ረገድ  ምንም ዓይነት በረራ ያልከለከለ መሆኑንና ትናንት የዓለም የምግብ ፕሮግራም በሁለት አውሮፕላኖች ወደ ትግራይ በረራ ለማድረግ ጥያቄ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡

ለሰብአዊ ድጋፉ ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች ላይ አስፈላጊ ፍተሻ  እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡

የበረራውን ሁኔታ ለማቀላጠፍም  ወደ ክልሉ  በረራ ማድረግ የሚፈልጉ አካላት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ ማግኘት  እንዳለባለቸው መገለጹን ከወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.