Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር ያላትን ፈርጀብዙ ወዳጅነትና አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር ጠንክራ ትሰራለች -አምባሳደር መለስ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም ከኬንያ ምክትል ፕሬዚደንት ዊሊያም ሳሞይ ሩቶ ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይቱ አምባሳደር መለስ ኬንያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነቷ ላበረከተችው አስተዋፅኦና ላሳያችው አጋርነት ለኬንያ ሕዝብና መንግስት ምስጋና አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር ያላትን ፈርጀ-ብዙ ወዳጅነትና አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር ጠንክራ ትሰራለች ብለዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚደንቱ ኢትዮጵያና ኬንያ በሁለት ሀገራት የሚኖሩ አንድ ሕዝቦች ናቸው ያሉ ሲሆን ÷በኢትዮጵያ የሚገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ኬንያን ጨምሮ ለቀጠናው ሀገራት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።
በግድቡ ላይ የሚካሄደውን የሶስትዮሽ ድርድር አስመልክተውም በኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን መካከል ያሉ አለመግባባቶች በአፍሪካዊ መፍትሄ ለአፍሪካዊ ችግሮች መርህ በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት በሚካሄደው የሶስትዮሽ ማዕቀፍ መፍትሄ ሊያገኝ እንደሚገባም ገልፀዋል።
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የተካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሠላማዊ መንገድ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት መግለፃቸውን ከኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.