Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከማላዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከማላዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይዘንሀወር መሰካካ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ እና ማላዊ የቆየ ታሪካዊ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
በቀጣይ ግንኙነቱ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና በዓለም አቀፍ መድረክም በሀገራቱ መካከል ትብብሮችን ለማጠናከር ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላትም ጠቅሰዋል፡፡
በትግራይ ክልል ተፈፀሙ የተባሉ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ተቋም የጋራ ምርመራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህን አዎንታዊ እርምጃ ከግምት ያላስገባ ጫና በማንኛውም መልኩ ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
የማላዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይዘንሀወ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በአቶ ደመቀ መኮንን በኩል ለተደረገላቸው ገለጻ ምስጋና ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ያላትን ግንኙነት አጠናክራ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኗንም ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.