የ6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ውጤት ማሳወቅ መርሃግብር በኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ተጀምሯል
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ውጤት ማሳወቅ መርሃግብር በኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ነው የተጀመረው።
የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ÷ ሀገራችን በብዙ ፈተናዎች ባለፈችበትና በስጋቶች ውስጥ የተካሄደው ምርጫ የዜጎችን ድምፅ የስልጣን ዋጋ ለመስጠት ተካሂዷል ብለዋል።
በዛሬው ዕለትም ምርጫ ያለፈበት ሂደትና ውጤቱ ይገለፃል ም ነው ያሉት።
ኢት ዮጵያ ሁልጊዜም በምርጫ ብቻ ስልጣን የሚያዝባት እንድትሆን ይሰራል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ህብረት ለምርጫ በታዛቢነት የነበረውን ሚና ገልጿል።
ህብረቱን በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ ታምራት ከበደ÷ ማህበራቱ ለዜጎች የመራጭነት ትምህርት መስጠታቸውን ተናግረዋል።
በዚህም በማህበራዊ ሚዲያ፣ በመገናኛ ብዙሃንና ገፅ ለገፅ ለዜጎች ግንዛቤ እንደተሰጠ ነው የገለፁት።
ህብረቱ ምርጫውን መታዘቡን የታዘበውን ውጤት ይፋ ማድረጉንም አቶ ታምራት አውስተዋል።
ህብረቱ 30 ሺህ ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ታዛቢዎችን አሰማርቻለሁም ማለቱም ተጠቅሷል፡፡
በአፈወርቅ እያዩና ሀቢብ መሀመድ