Fana: At a Speed of Life!

በጁባ ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ተወካዮች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን ጁባ በጁባ ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ተወካዮች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በዚህ ማብራሪያ ላይ ከተለያዩ የዳያስፖራ ማህበራት እና የአደረጃጀቶች የተውጣጡ አመራር ተወካዮች ተገኝተዋል።
በዚህም መንግስት በትግራይ ክልል የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ ላይ እና የመከላከያ ሠራዊቱን ማስወጣትን የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱ ተነግሯል።
በዚህ ገለጻ ላይ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ÷ውሳኔው ቅፅበታዊ ውሳኔ ሳይሆን በመንግስት ብዙ ውይይትና ጥናት በማድረግ የተወሰደ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል።
ለውሳኔው መነሻ የሆኑ መሠረታዊ ምክንያቶችም ወቅቱ የእርሻ ጊዜ በመሆኑ የትግራይ አርሶ አደር ተረጋግቶ በግብርና ሥራው ላይ እንዲያተኩር ለማድረግ እና ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልገው ህዝብም ድጋፉ በትክክል እንዲደርስ፣ ለህዝቡም የጽሞና ጊዜ መስጠት አስፈላጊ ነው ከሚል እሳቤ እንደሆነ አስረድተዋል።
የማህበረሰቡ አባላት በማህበራዊ ሚዲያ በሚናፈሰው ፍጹም ከእውነት የራቀ መረጃ መሸበር እንደማይገባና ከአገር ጎን በመቆም የኢትዮጵያን ስም ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን መታገል እንዳሚገባ አስገንዝበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው÷ የተሰጣቸው አሁናዊ ገለፃ እጅግ አስፈላጊና ወቅቱን የጠበቀ በመሆኑ አመስግነዋል።
ጥያቄዎችን በማንሳት ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን÷ ለወደፊቱም ተመሳሳይ መረጃዎችን የመስጠቱ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
በመጨረሻም የማህበረሰቡ አባላት ያላቸው የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ በኢትዮጵያ አንድነት እና በብሔራዊ ጥቅማችን ዙሪያ በጋራ እንቆማለን ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
168
Engagements
Boost Post
150
1 Comment
9 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.