Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊና ሁሉን አካታች ምርጫን ለማካሄድ የሚተገበሩ ስራዎችን ተመድ ያደንቃል-ሞሪን አቺንግ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ንግግር ያደረጉት ሞሪን አቺንግ ተመድ ለምርጫው የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል።

በዚህም ሙያዊ እንዲሁም ቁሳዊ ድጋፍ በስሩ በሚገኙ  ስድስት አጋሮች ማድረጉን አንስተዋል።

ባለፉት ሁለት አመታት የምርጫውን ሂደት ሲከታተል ቆይቷልም ነው ያሉት።

አሁንም ስድስተኛው ምርጫ ሙሉ በሙሉ ባለማለቁ  ጳጉሜ ላይ በሚደረገው ምርጫ ድጋፋችን ይቀጥላል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊና ሁሉን አካታች ምርጫን ለማካሄድ የሚተገበሩ ስራዎችን ተመድ ያደንቃልም ነው ያሉት።

በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አዎር በበኩላቸው የምርጫው ሂደት ለነበረው ሰላማዊነት አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

ዲሞክራሲ ሂደት ነው ያሉት አምባሳደሩ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት።

በአፈወርቅ እያዩና ሀቢብ መሀመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.