Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የመራጩን  ህዝብ ትግስት በማድነቅ  ለተሳትፏቸው ከፍ ያለ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ  ነው ምርጫውን ያደረገው ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ  ተናገሩ።

የፀጥታ መደፍረስ፣ የኮቪድ 19፣ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ፈታኝ ቢሆንም በተሻለ መፈፀም ተችሏል ብለዋል።

በፈታኝ ሁኔታ የተካሄደው ምርጫ እንደተሟረተበት ሳይሆን በተሻለ አፈፃፀም ተካሂዷል፣ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ።

ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲከናወን  ስላደረጋቸው ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል ፕሬዚዳንቷ፡፡

በተገለፀው ውጤት ላሸነፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ርዕሰ ብሔሯ የተሸነፋችሁ ይህ የመጨረሻ ምርጫ አለመሆኑን ልትገነዘቡ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በምርጫው መሳተፍ በራሱ ድል ነውም ሲሉ አክለዋል።

በትጋት ለመረጠው ህዝብም አክብሮታቸውን ገልፀዋል።

በምርጫው ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና በመውጣቷ እንኳን ደስ አለንም ነው ያሉት።

በሰላማዊ መንገድ ከምርጫ እራሳቸውን ያገለሉ ወገኖች በቀጣይም የመነጋገር ሂደቱ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምርጫ የዲሞክራሲ ግንባታ መንገድ ነው ብቸኛው ግን አይደለም ያሉት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ለድህረ ምርጫ ስራዎች ትኩረት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

ተመርጦ መንግስት የሚሆነው ፓርቲም ሁሉን ኢትዮጵያዊያንን እኩል ማገልገል እንዳለበትም አሳስበዋል።

የአስተሳሰብና የአደረጃጀት ስብጥር እንዲኖረውም የምርጫ ህጉን መፈተሽና መመርመር እንደሚያስፈልግ አክለዋል።

የመራጩን  ህዝብ ትግስት በማድነቅ እና ለተሳትፏቸው ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ለሀገር መረጋጋትና ሰላም ቅድሚያ እንዲሰጥ፣ ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት ፈታኝ ሁኔታ ለማውጣት እንዲሰራም ጠይቀዋል።

ሀገር ተከብራ የምትኖረው ስንነጋገርና ስንደማመጥ፣ ብሔራዊ መግባባት ሲኖረን ነውም ብለዋል። ለዚህም ሁሉም እንዲሰራ ጠይቀዋል።

እንከን የለሽ ፖለቲካና ምርጫ ሊኖር አይችልም ያሉ ሲሆን÷ ለመሻሻሉ የሁሉንም ጥረት እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.