Fana: At a Speed of Life!

2 ሺህ 573 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)2 ሺህ 573 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎች በየቀኑ ወደ አገራቸው እየተመለሱ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት 118 ሴቶችንና 72 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 573 ዜጎች ወደ አገራቸው ገብተዋል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን የያዘው ኮሚቴ አቀባበል እንዳደረገላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.