በመዲናዋ 1 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀምበር ለመትከል የሚያስችል ንቅናቄ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)”አዲስ አበባ 1 ሚሊየን ችግኝ ትተክላለች ትንከባከባለች “በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር በሁሉም ክፍለ ከተሞች በመካሄድ ላይ ይገኛል ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከነዋሪዎች ጋር በመሆን በአራዳ ክፍለ ከተማ በመገኘት አሻራቸውን አኑረዋል።
በአንድ ጀምበር 1 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐግብር ኢትዮጵያን አረንጓዴ በማልበስ ባሻገር ምግባችንን ከደጃችን ለማምረት በየአመቱ በልዩ ሁኔታ የምንሰራው ተግባር ነው ሲሉም ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል ።
ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ስራ የሁልጊዜም ተግባር መሆን እንዳለበት ገልፀው ነዋሪዎችም አካባቢያቸውን አረንጓዴ በማድረግ እና የተተከሉ ችግኞችን ዘውትር መንከባከብ እንዳለባቸው ጥሪ ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በከተማዋ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ለመትከል በእቅድ ከተያዘው 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞች ውስጥ ከ5 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!