Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት መርሃ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት መርሃ ግብር ተጀምሯል።

መርሃ ግብሩ በቢሾፍቱ ከተማ የተጀመረ ሲሆን÷ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይም አመራሮቹ የቡኡረ ቦሩ ትምህርት ቤትን ግንባታ አስጀምረው የችግኝ ተከላም አካሂደዋል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመርሃ ግብሩ በሁሉም በክልሉ አከባቢዎች ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል በማሳተፍ 3ሺህ ቡኡረ ቦሩ ሙዋለ ህፃናቶችን ለመገንባት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ለተገነቡት ኢፈ ቦሩ ትምህር ቤቶች መፅሀፍቶችን ለማሰባሰብ መታቀዱን አንስተው ህዝቡም በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ክልሉ ባለሀብቶችንና ማህበረሰቡን በማነቃነቅ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን በመገንባት፣ መፃህፍትን በማሰባሰብና መሰል ስራዎችን በመስራቱ አመስግነው ሌሎች ክልሎችም በተመሳሳይ ባለሀብቶችንና ማህበረሰቡን በማነቃነቅ በትኩረት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል ።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ በበኩላቸው ÷በክልሉ በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት 34 ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን፣ ቤተ መፃህፍቶችንና ቤተ ሙከራዎችን ጨምሮ ከ 5 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የዜግነት አገልግሎት ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

በትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.