Fana: At a Speed of Life!

1ነጥብ 2ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው 48 ፕሮጀክቶች በዱከም ከተማ ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)1ነጥብ 2ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው 48 ፕሮጀክቶች በዱከም ከተማ ተመርቀዋል።

ፕሮጀክቶቹ ኢፈ ቦሩ ትምህርት ቤትን ጨምሮ የጤና ተቋማት የአረንጓዴ ስፍራዎች ፖርኮች የንፁህ መጠጥ ውሀ እና መሰል 48 ፕሮጀክቶች ናቸው።

በምርቃ ስነስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያን ጨምሮ የተለያዩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድሩ በዘንድሮ ዓመት በመንግስት እና በህዝቡ ተሳትፎ ከ11ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን አንስተዋል።

ይሄም ክልሉ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ተሰርተው እንዲጠናቀቁ በየደረጃው የስራ አቅጣጫ በመስጠትና ክትትል በማድረግ በመሰራቱ ፕሮጀክቶቹ በአጭር ጊዜና በጥራት መጠናቀቃቸውን ገልፀው፥ ህብረተሰቡ ፕሮጀክቶቹን በባለቤትነት ስሜት ሊጠብቃቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

የዱከም ከተማ ከንቲባ አቶ ተሾመ ግርማ፥ ከተማ አስተዳደሩ በዘንድሮ ዓመት በሁለት ዙሮች 48ፕሮጀክቶችን አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሲያደርግ ገቢን በማሳደግና ህብረተሰቡን እና ባለሀብቶችንም ጭምር በማስተባበር መሆኑን አንስተዋል።

በትዝታ ደሳለኝ

ምስል – ኢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.