Fana: At a Speed of Life!

ኢዜማ ለዘይሴ ህዝብ ያዘጋጀው የምስጋና ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ለዘይሴ ህዝብ ያዘጋጀው የምስጋና ስነ-ስርአት እየተካሄደ ይገኛል።

የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ በስነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት፥ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ፓርቲያቸው ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

ኢዜማ ዜጋ ተኮር ፌዴራሊዝም ርዕዮተ ዓለም የሚከተል ፓርቲ በመሆኑ ማህበራዊ ፍትህን ለማስፈን እንደሚሰራ ተናግረዋል።

እንደታሰበው ብዙ የምርጫ ክልሎች ላይ ፓርቲው እንዳላሸነፈ ገልጸው፥ “ካሸነፍንባቸው ጥቂት አካባቢዎች አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የዘይሴ ልዩ ምርጫ ክልል አንዱ በመሆኑ ለህዝቡ ምስጋና ለማቅረብ መድረክ ተዘጋጅቷል” ብለዋል።

ምርጫው በአግባቡ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የህዝብን ድምፅ በፀጋ ለመቀበልና ችግሮችንም በህጋዊ መንገድ ብቻ ለመፍታት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

በምርጫው ምክንያት ሀገርና ህዝብ አደጋ ላይ መውደቅ እንደሌለባቸው አስገንዝበዋል።

“የመረጠን የዘይሴ ህዝብ ምስጋና ይገባዋል” ያሉት አቶ የሺዋስ፥ መንግስትን ጨምሮ የምርጫ አስፈፃሚዎችና ታዛቢዎች ለምርጫው ሰላማዊነት ላበረከቱት አስተዋፅኦ አመስግነዋል።

እንደኢዜአ ዘገባ በስነ-ስርዓቱ ላይ የኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዘይሴ ህዝብ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.