ዓለምአቀፋዊ ዜና

በደቡብ አፍሪካ የኮቪድ 19 እንቅስቃሴ ገደብ ተራዘመ

By Alemayehu Geremew

July 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ የኮቪድ 19 ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ዜጎች ለቀጣይ ሁለት ሳምንታት በቤታቸው እንዲቆዩ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ተሰምቷል፡፡ ፕሬዚደንቱ ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ እንዲቆዩ ትዕዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን፥ የምሽት እንቅስቃሴ ላይም የተጣለው ገደብ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የአልኮል መጠጥ ሽያጭ መፈፀምና ስብሰባዎችን ማካሄድም ክልክል ሆነው እንደሚቀጥሉ ነው የተገለፀው፡፡

በሌላ በኩል ዜጎች ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲገለገሉ ለምግብ ቤቶች እና ለአንዳንድ የአካል እንቅስቃሴ መስሪያ ቦታዎች ፈቃድ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡

በእንቅስቃሴ ገደቡ የተጎዱትን በርካታ የንግድ ተቋማትን ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስት የኮቪድ 19 የእርዳታ ፈንድ ያራዝማልም ነው ያሉት ፕሬዚደንቱ ፡፡

ደቡብ አፍሪካ እሁድ ቀን ብቻ 16 ሺህ 302 አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ዜጎች የመዘገበች ሲሆን፥ ይህም በሃገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ዜጎችን ቁጥር 2 ሚሊየን 195 ሺህ 599 ያደርሰዋል ተብሏል፡፡ በዚሁ ቀን የ151 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፥ አጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥርም 64 ሺህ 289 ደርሷል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!