Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሩሲያ በወታደራዊ ቴክኒክ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ሩሲያ በወታደራዊ ቴክኒክ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ በማተኮር ለሶስት ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩት ውይይት የተለያዩ ስምምነቶች ላይ በመድረስ ተጠናቋል።
ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው ይህ ውይይት በ10ኛው የጋራ ውይይት ላይ የተደረሱ ስምምነቶች አተገባበርን በጥልቀት ተመልክቷል።
አሁን የተደረሰው ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት ይበልጥ የሚያጠናክርና ይበልጥ በማቀራረብ አብሮ መስራት የሚያስችል መሆኑን የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ሊዊጅ ገልፀዋል።
የሰራዊቱን አቅም በእወቀት ፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ ለማዘመን ለሚደረገው ጥረትም የሁለቱ ሃገራት ስምምነት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
በውይይቱ ከሩሲያ ፌዴሬሽን ወታደራዊ ሃይል የቴክኒክ ዘርፍ የተለያዩ ተቋማትና ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.