Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ ትግራይ የላከው ሰብዓዊ እርዳታ መቐለ ደርሷል

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች የሚውል የመጀመሪያው ዙር የሰብዓዊ እርዳታ መቐለ መድረሱን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡
መንግስት ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እርዳታ እንዲያቀርቡ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ባሳለፍነው ሳምንት ከ40 የሚበልጡ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ክልል መንቀሳቀሳቸው ይታወቃል፡፡
በዛሬው ዕለትም በክልሉ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች የሚውል የመጀመሪያው ዙር የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች መቐለ መድረሳቸውን በዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡
ድርጅቱ በክልሉ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል 1 ሺህ ሜትሪክ ቶን የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የገለጸው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.