የሀገር ውስጥ ዜና

ከ500 ሺህ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የተገዛው የቆጣሪ መመርመሪያ መሳሪያ አገልግሎት ላይ ሊውል ነው

By Tibebu Kebede

July 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከ500 ሺህ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የገዛው ዘመናዊ የቆጣሪ መመርመሪያ መሳሪያ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

በተቋሙ የማዕከላዊ ሜትር ማኔጅመንት ሲኒየር ኤሌክትሪካል ኢንጂነር አቶ መሳይ መኮንን እንደገለጹት፥ መሳሪያው ከፖላንድ ግዢ ተፈፅሞ በሁለት ዙር ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ነው፡፡

መሳሪያው በባለሙያዎች ከተገጠመ በኋላ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ብለዋል፡፡

ሜትር ቴስት ቤንች የተሰኘው ይህ መሳሪያ ከቆጣሪ ምርመራ ጋር ተያይዞ ያሉትን አጠቃላይ ስራዎች የሚያግዝ ሲሆን፥ አዳዲስ ቆጣሪዎች ሲገዙ ወደ አገልግሎት ከመግባታቸው በፊት ለመመርመርና በተቋሙ መስፈርት መሰረት መሟላታቸውን ለማረጋገጥ ያስችላል ተብሏል፡፡

ለመሳሪያው ግዢ ፓወር አፍሪካ 297 ሺህ 120 ዶላር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ቀሪው ገንዘብ በተቋሙ መሸፈኑን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!