ስፓርት

የማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ላስመረጣቸው አትሌቶች ሽኝት አደረገ

By Tibebu Kebede

July 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ላስመረጣቸው አትሌቶች ሽኝት አደረገ።

በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው ከሚሳተፉት አትሌቶች መካከል ፌዴራል ማረሚያ አምስት አትሌቶችን አስመርጧል።

በዛሬው እለትም አትሌቶቹን ውጤት እንዲያስመዘግቡ በማበረታታት ሽኝት አድርጎላቸዋል።

የፊደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ዳመና ዳሮታ በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክት በውድድሩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውጤታማ እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የክለቡ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ያረጋል አደመ ክለቡ ከባርሴሎና ኦሊምፒክ ጀምሮ በተለያዩ የኦሊምፒክ መድረኮች በርካታ አትሌቶችን በማሳተፍ ውጤት ማስመዝገቡን አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የማረሚያ ቤት ስፖርት ክለብ ለአትሌቲክሱ ውጤታማነት ትልቅ መሰረት የጣለ እንደሆነ መግለጿን ኢዜአ ዘግቧል።

ክለቡ በማራቶን አትሌት ሮዛ ደረጀና ትዕግስት ግርማ፣ በ10 ሺህ ሜትር አትሌት ጸሀይ ገመቹ፣ በ5 ሺህ ሜትር አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ እንዲሁም በ3 ሺህ መሰናክል አትሌት ሃይለማሪያም አማረ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ሃገራቸውን እንዲወክሉ አስመርጧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!