ዓለምአቀፋዊ ዜና

በኢራቅ በኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከል በተነሳ እሳት ከ50 በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

By Tibebu Kebede

July 13, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢራቅ በኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከል በተነሳ እሳት ከ50 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ፡፡

አደጋው ናሲሪያ በተባለችው ከተማ በሚገኘው አል ሁሴን ሆስፒታል የደረሰ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በሆስፒታሉ የሚገኝ ኦክስጅን መፈንዳት ለአደጋው መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረም ነው ፖሊስ የገለጸው፡፡

ማገገሚያ መዕከሉ ከሶስት ወራት በፊት የተገነባ ሲሆን፥ 70 ታካሚዎችን ማስተናገድ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

አደጋው በደረሰበት ወቅትም 63 ታካሚዎች ሆስፒታሉ ውስጥ ነበሩ ተብሏል፡፡

አደጋውን ተከትሎ በአካባቢው ተቃውሞ መቀስቀሱን የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!