Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማእከላዊ ሪጅን ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ኪዳኔ መንገሻ የተፈራረሙ ሲሆን ÷ስምምነቱ ደንበኞች ወደ ባንኩ የሚያመጡት የውክልና ሰነድ ትክክለኛ መሆኑን ከኤጀንሲው መረጃ ቋት በቀጥታ የሚያረጋግጡበት መሆኑ ታውቋል፡፡
አቶ ኪዳኔ መንገሻ ስምምነቱ በሁሉም የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ተግባራዊ መሆን የሚችል መሆኑን ገልፀው÷ ደንበኞችን ከውጣውረድና ከአላስፈላጊ ወጪ ይታደጋል፣ጊዜ ቆጣቢና ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ሀሰተኛ ውክልና ሰነድ ወደ ባንኩ በማምጣት የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ ለማውጣት የመሞከር ወንጀልንም ይከላከላል ነው ያሉት፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው÷ ኤጀንሲው ከሚሰጣቸው ከ50 በላይ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች 20 አምስቱን በቴክኖሎጂ አስደግፎ የሚሰጥና የውክልና ውል ከፍተኛ ተገልጋይ ያለው አገልግሎት መሆኑን መግለፃቸውን ከፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.