Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2013 በጀት ዓመት ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ከህዝብ መሰብሰቡን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ከሐምሌ 1/2012 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 /2013 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ለግድቡ 2 ቢሊየን 49 ሚሊየን 85 ሺህ 105 ብር ከህዝብ መሰብሰቡን የፅህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም ተናግረዋል።

ከሀገር ውስጥ ቦንድና ስጦታ 1 ቢሊየን 767 ሚሊየን 383 ሺህ 208 ብር የተሰበሰበ ሲሆን ከውጭ ሀገር ዲያስፖራ ቦንድ ሽያጭ እና ስጦታ 134 ሚሊየን 96 ሺህ 860 ብር መገኘቱንም ኃላፊው ገልጸዋል።

በተጨማሪም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ8100 አጭር የሞባይል መልእክት አገልግሎት 132 ሚሊየን 853 ሺህ 752 መቶ ብር መገኘቱንም አቶ ኃይሉ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት የግድቡ ሁለተኛ ዙር ሙሌት እየተካሄደ ሲሆን አሁን ያለውን የህዝብ ተነሳሽነት ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ እንዲውል የተለያዩ እቅዶች ተነድፎ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ እስካሁን ከህዝብ የተሰበሰበው የገንዘብ ድጋፍ 15 ቢሊየን 729 ሚሊየን ብር በላይ መድረሱን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ማስታወቁን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.