በሶማሌ ክልል የሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት መሰረቱ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የሚፎካከሩ አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት መሰረቱ ፡፡
የጋራ ምክር ቤቱን የመሰረቱት የሶማሌ ብልፅግና፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ፣ ነፃነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ እና የምዕራብ ሶማሌ ዴሞክራሲ ፓርቲዎች ናቸው።
የሶማሌ ብልፅግና ፖርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ፈይሰል ረሺድ÷በሰለጠነ ፖለቲካዊ እሳቤ እንደ ክልልም ሆነ ሀገር አቀፍ ባሉ አጀንዳዎች ላይ እንዲሁም አንድ በሚያደርጉና በሚያቀራርቡ ፖለቲካዊ ሐሳቦች ላይ በጋራ ለመስራት ከመግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል ።
ምክር ቤቱ የፊታችን ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደ ክልል በሚደረገው ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በየሁለት ሳምንቱ ሁሉም ፓርቲዎች እየተገናኙ እንደሚሰበሰቡና እንደሚሰሩ ጠቁመዋል፡፡
ምክር ቤቱ ከምርጫው በኋላ ዘላቂ ሆኖ እንደሚቀጥልአቶ ፈይሰል መግለጻቸውንም ከሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!